ጥይት ፋብሪካው ወደ እስር ቤት ተለወጠ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአምቦ እና አካባቢዋ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሚታሰሩ ወጣቶች ቁጥር በመጨመሩ፣ ከአምቦ ወጣ ብሎ የሚገኘው የጥይት ፋብሪካ ወደ እስር ቤት መለወጡን ምንጮች ገልጸዋል።
በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጥይት ፋብሪካው ግቢ ታስረው የሚገኙ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል።
በሌላ በኩል መንግስት የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎችን “በመሰብሰብ ህዝባዊ ተቃውሞው እንዲበርድ አስተዋጽኦ አድርጉ ፣ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ግን በተናጠል እርምጃ እንወስዳለን፣ መንገዶች የሚዘጋጉ ከሆነ አውሮፕላን እንጠቀማለን ” እያሉ በማስፈራራት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።