ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የ68 አመቱ ጆን አታሚልስ ትናንት ካረፉ በሁዋላ፣ ጆን ማሀማ ፕሬዚዳንት በመሆን ዛሬ ቃለመሀላ ፈጽመዋል።
ተቃዋሚዎች ሰላማዊውን የስልጣን ሽግግር ያደነቁ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱም ሁሉንም ጋናውያንን በእኩል እንደሚያገለግሉ እና ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረዋል።
የአለም መሪዎች ለሟቹ ፕሬዚዳንት ያላቸውን አድናቆት እየገለጡ ነው። የላይቤሪያዋ መሪ፣ ፕሬዚዳንቱ የተለየ ስእብና ባለቤት መሆናቸውን ሲናገሩ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በባራ አኦባ በበከኩለአወ ፣ ጠንካራ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ብለዋቸዋል።
የፕሬዚዳንት አታ ሚልስ ዜና እረፍት እንደተሳማ ኢትዮጵያውያን የመሪያቸውን የጤንነት ሁኔታ በድጋሜ መጠየቅ ጀምረዋል።
ጋና የፕሬዚዳንቱዋን ዜና እረፍት ይፋ ስታደርግ፣ የአቶ መለስ የጤንነት ሁኔታ ግን እስካሁን ታላቅ ሚስጢር እንደሆነ ነው።
ፎርቹን ጋዜጣ አቶ መለስ ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል ብሎ ሲዘግብ ሪፖርትር ደግሞ አቶ መለስ በውጭ አገር እረፈት እያደረጉ ነው ብሎአል።
_____________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide