ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልክ የሚታገዙ ወንጀሎችን፣ ማጭበርበርን እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ደንበኞች የሚገለገሉባቸውን ሲም ካርዶች ባለማስመዝገባቸው 349 ሺ 261 ሲምካርዶች ከአገልግሎት ውጭ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት አስታውቋል።
የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚንስትር ዶ/ር ደብረ ፅዩን ገ/ሚካኤል ፣ ሲም ካርዶቹ ከአገልግሎት ውጭ ከመሆናቸው በፊት ሰነድ የሌላቸውን የሲም ካርድ ባለቤቶች ለመመዝገብ ፣ በአሁኑ ስዓት ማንነታቸው በማይታወቁ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ግንኙነት የሚያደርጉ ቶሎ ማንነታቸውን እንዲያስታውቁ እየተናገሩ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በማይመዘገቡት እና ማንታቸው ባልታወቁ ደንበኞች ላይ የመዝጋት እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።
እ.ኤ. አ ከመስከረም ወር 2017 አካባቢ ጀምሮ የሲም ካርዶቹ ከአገልግሎት ውጭ ከመሆናቸው በፊት ለደንበኞች የሁለት ዓመት የምዝገባ ጊዜ ተሰጥቷቸው በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቢያስመዘገቡ የሚል ሃሳብ የቀረበላቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ፣ “ድምፃቸውን እየሰማነው ጊዜ ለመስጠት ጊዜ መወሰዱን አንቀበለው” ብለዋል፡፡