መስከረም ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በኦሮምያ እና በአዲስ አበባ አካባቢዎች የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል።
በአማራ ክልል ህዝባዊ ንቅናቄዎች በሚካሄዱበት ወቅት በተመሳሳይ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል።
በአዲስ አበባ እና ዙሪያ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የፎቶ ግራፍ እና የቪዲዮ መልክቶችን መላክ አለመቻላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ፍጥነት ቢቀንስም የኢንተርኔት አገልግሎት መኖሩ ታውቋል።