ጄኔራል ማሾ በየነ ከምስራቅ አዛዥነት ስልጣናቸው ተነሱ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሶማሊው ክልል ፕሬዚዳንት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ማዕሾ በየነ ደስታ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ታውቋል። ጄኔራሉ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው መሄዳቸውንም ምንጮች ተናግረዋል። በሶማሊ ክልል ከፍተኛ የሆነ የሙስና ሰንሰለት የዘረጉት ጄኔራል ማዕሾ ከክልሉ መነሳታቸው፣ ለአብዲ አሌ አገዛዝ መልካም ዜና አይደለም ተብሏል። የጄኔራል ማዕሾ ምክትል የነበረው ጄኔራል አማረ፣ቀድም ብሎ ከስልጣን መነሳቱ ታውቋል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአሶሳ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ፖሊሶች መያዛቸው ታውቋል። ፖሊሶቹ በከተማው ለተገደሉት ከ15 ያላነሱ ሰዎች ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ተብሏል። አብዛኞቹ ሰዎች በእነዚህ የከተማው ፖሊሶች መገደላቸውን ያነጋገርናቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት ከተማውን መከላከያ መቆጣጠሩም ታውቋል።