ኢሳት (ሃምሌ 25 ፥ 2008)
ይህ በእንዲህ እንዳለም የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ያነሱ የኮሚቴ አባላትን በማሳደድና በማሰር ላይ የሚገኘው የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በዋሽንግተን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው።
ዕሁድ ሃምሌ 24 ፥ 2008 ዋሽንግተን ዳለስ ዓለም አቀፍ አውሮፓላን ማረፊያ ሲደርሱ እንግዳ መቆየ ስፍራ ላይ ተቃውሞ የጠበቃቸውን ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ በሁኔታው ሲደናገጡ ታይተዋል።
በዕለቱ ዋሽንግተን እንደሚገቡ መረጃ የደረሰው የዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ላይ ተቃውሞን ሲገልፁ የሚያሳየው ቪዲዮም በኢሳት በኩል መሰራጨቱ ይታወቃል።