መጋቢት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር መረራ ጉዲና የዋስትና መብት መከልከላቸውን አስመልክቶ እየተፈጸመባቸው ያለውን የመብት ጥሰቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ እዲያውቅላቸው ከእስር ቤት ደብዳቤ ልከዋል። የተከሰስኩት ምንም ዓይነት ሕገወጥ ወንጀል ፈጸሜ ሳይሆን ለዘመናት ለአገሬና ለህዝብበመታገሌ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ ብለዋል።
ከእነ ጀነራል መንግስቱ ነዋይ እና ጄኔራል ታደሰ ብሩ ዘመን ጀምሮ ከአንድ ትውልድ በላይ ገዳዮችና ሟቾች፣ ታሳሪዎች እና አሳሪዎች፣ በበዙበት የሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ የቆየሁት አንድከሆዱ በላይ ለሀገሩ የሚያስብ ምሁር ማድረግ ያለበትን ለማድረግ ከ45 ዓመታትበላይ ለሀገሬ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ በታማኝነት መታገሌ ነው። ይህም እየታወቀ ወደ ጎን መገፋቱ ለሁላችንም የምትሆንና በእኩልነት የምታስተናግደን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠርናነጻ የፍትህ ስርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን ላለፉት 25 ዓመታት በመታገሌመከሰሴ አንሶ፣ የሀገሪቱ ፓርላማ አባል ጭምር የነበርኩ ሰው ለተራ ወንጀለኛ የሚፈቀድ የዋስ መብት በመከልከሌ የተሰማኝ ጥልቅ ሀዘን ለራሴ ብቻ ሳይሆን እኛም ሆንን ልጆቻችን በሰላም ይኖሩባታል በምንለው መከረኛ ሀገራችንና አላልፍለት ብሎ ለታመሰው ለመላውመከረኛ ህዝባችን ጭምር መሆኑ እንዲታወቅልኝ። ሲሉ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳውቀዋል።
በትናንትናው እለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የዋስትና መብት ውድቅ በማድረግ በዋስትና ቢወጡ መረጃ በማሸሽ ከሀገር ይወጣሉ በሚል ምክንያት የዋስትና መብት እንዳያገኙ ተከልክለዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲናበኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በአውሮፓ ህብረት ባደረላቸው ጥሪ መሰረት ቤልጅየም ደርሰውሲመልሱ በኮማንድ ፖስቱ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው መወሰዳቸው ይታወሳል።