ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች የታየው ዝናብ እጥረትና የተከሰተው ድርቅ ኢሊኖ እየተባለ የሚጠራው የአየር መዛባት የፈጠረው ነው ብሎአል። በተለያዩ አካባቢዎች የእንስሳት መኖና እና የምግብ እጥረት ተፈጥሯል ብሎአል።
ሚኒስቴሩ በውጭ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን የችግሩን አሳሳቢነት ይፋ ማውጣታቸውን ተከትሎ የሰጠው የመጀመሪያ መግለጫ ነው። ገዢው ፓርቲ አገሪቱ በምግብ ራሱዋን መቻሉዋን በተደጋጋሚ ሲናገር ቢሰማም ፣ የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም ችግሩ ይፋ መውጣቱ፣ በግብርናው ዘርፍ ተገኘ የሚባለው ስኬት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከመዋል ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
የምግብ እጥረት እና የምግብ ዋጋ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተከሰተ ሲሆን፣ በተለይ በመጪው መስከረም የእንስሳት ምርቶች እና እህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል የውጭ ድርጅቶች በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።