ሰኔ 15 ፥ 2009
በኢትዮጵያ ግዙፉን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ሊዘጉት እንደሚችሉ ታዋቂው የናይጄሪያ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ አስጠነቀቁ።
ባለሃብቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሲሚንቶ አምራቹ ኩባንያቸው የተወሰነ ሥራቸውን ለወጣቶች እንዲሰጡ ትዛዝ ከሰጡ በኋላ ነው።
ናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊስ ዳንጎቴ የኦሮሚያ መንግስት ይህንን ትእዛዙን ካላነሳ ፋብሪካውን ዘግተው ሥራውን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ እንደሚያስወጡ ዝተዋል። የኦሮሚያ ምስራቅ ዞን አስተዳደር የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የአዋሽ የሸክላና የፑሚስ ሥራዎችን ለወጣቶች ስለሰጠ በፋብሪካው ላይ ለሚደርስ ችግር ኃላፊነቱን አንወስድም በማለቱ እንዳስቆጣቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል አረጋግጧል።
አስተዳደሩ ይህንን በተመለከት ደብዳቤ ለዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አመራሮች መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል።
ደብዳቤው የኦሮሚያ ወጣቶችን ሥራ የማስያዝ ስላልተቻለ በአካባቢው ለሚቀሰቀሰው አመፅና በፋብሪካው ላይ ለሚደርሰው ጉዳት አስተዳደር ሐላፊነት እንደማይኖረው በማተት ዳንጎቴ ፋብሪካን አስጠንቅቋል።
የዳንጎንቴ ዋና ሥር አስፈፃሚ ኤድዊን ዴቫኩመር ግን የማዕድን የሕንፃና የኤክስካቫተር ሥራዎችን ለሌላ አሳልፎ መሰጠት ድርጅታቸውን ለውድቀት ስልሚያጋልጣቸው ሥራውን ለኦሮሚያ ወጣቶች አሳልፈው እንደማይሰጡ ገልፀዋል።
እናም የኢትዮጵያ መንግስት ጣልቃ ገብቶ የኦሮሚያን ትዕዛዙ እንዲቆም ካላደረገ ዳንጎንቴ ሲሚንቶ ፋብሪካን ዘግቶ ከሀገር እንደሚወጣ አስታውቋል።
ለዚህም የግዙፉ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት ታዋቂው የናይጄሪያ ባለሀብት አልስ ዳንጎቴ ይህንኑ በሚመለከት ለመጨረሻ ጊዜ ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ እንደሚፅፉ ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሊር ኡማ በበኩላቸው የባለሀብቱን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ይሁንና ማንም ባለሀብት ፈልጎ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ሁሉ ሳይፈልግ ሲቀርም መቅረት ይችላል ሲሉ የዳንጎንቴን ማስጠንቀቂያ አጣጥለዋል።