(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/2010) የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ጦርነቱን አቁማ የሰላም ድርድሩን እንድትፈርም የአንድ ወር ቀነ ገደብ አስቀመጠ።
ሃገሪቱ ያንን የማታደርግ ከሆነ ግን የከፋ ማዕቀብ ሊጠብቃት ይችላል ብሏል።
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ ነበር ደቡብ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ የጀመረችው።
ለአስር ሺዎች ሞትና ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት የሆነው ይህ የእርስበርስ ጦርነት ለእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሳይቀር አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።
በተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የተጠራውና እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ቀነ ገደብን ያስቀመጠው ውይይት ደቡብ ሱዳን እስከ አንድ ወር ድረስ የሰላም ስምምነቱን እንድትፈርም ያስገድዳል።
ሃገሪቱ በአንድ ወር ውስጥ ይህንን ማድረግ ካልቻለች ግን የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሌላ ከበድ ያሉ ማዕቀቦች ይጠብቋታል ይላል የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት።
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን የማያከብሩ ከሆነ ግን ሀገሪቱ ላይ መአቀብ እንደሚጥል ነው ያሳወቀው።
ስምምነቱን በተመለከተም ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስጠነቅቃል።
ይህ የተባበሩት መንግስታት ውሳኔ ከመንግስታቱ ድርጅት 9 ድምጽ ማግኘት የሚጠበቅበት ሲሆን በእስካሁኑ ሂደት 6 ድምጽ ማግኘቱ ተመልክቷል።