ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዴ ጠበቅ ሌላ ጊዜ ላላ ሲል የቆየው የደቡብ ሱዳን ግጭት መልሶ ማገርሸቱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች
ያሳያሉ። ዩኒቲ ስቴት በሚባለው ግዛት የተጀመረው ጦርነት በቅርብ ጊዜ ከተደረጉት ሁሉ የከፋ ነው ተብሎአል። የኢጋድ አገሮች በአዲስ አበባ የተፈረመውን
የሰላም ስምምነት በማይቀበሉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ በሚዝቱበት ሰአት ግጭት መቀስቀሱ፣ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች በኢጋድ ሽምግልና ላይ
አለመተማመናቸውን እንደሚያሳይ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። በርካታ የአማጺው ቁስለኞች በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን
መዘገባችን ይታወሳል።