ደቡብ ሱዳናውያን የአፍሪካ ሕብረት ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራቸው እንዳይገባ ጠየቁ

ሐምሌ  ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጁባ በተካሄደው ተቃውሞ ዜጎች ተጨማሪ ጦር ወደ አገራችን እንዲገባ አንፈልግም ብለዋል።

በድጋሜ እንደ አዲስ ያገረሸውን የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነትን ተከትሎ  ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳና ሱዳን ሰራዊታቸውን ለመላክ ተዘጋጅተዋል። ውሳኔውን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አውግዘውታል።

”እኛ አንድም ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራችን እንዲገባ አንፈልግም። ወታደር መላክ  መፍትሄ አያመጣል” ሲሉ  የደቡብ ሱዳን ቃል አቀባይ የሆኑት ሚካኤል ማኩዬ ማስጠንቀቂያ  መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።