(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 29/2010) አንጋፋው ደራሲ አሰፋ ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በ1928 አዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት አቶ አሰፋ ገብረማርያም |
የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት መከታተላቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
ከፍተኛ ትምህርታቸውን በቀድሞው ሶቪየት ኀብረት ሌኒን ግራድ ዩኒቨርሲቲና በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ኢንደንብራ ዩኒቨርስቲ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አቶ አስፋ ገብረማርያም “የመስከረም ጮራ”እና “The Voice” የተሰኙ የግጥም መድብሎች ን ጨምሮ በርካታ የስነጽሁፍ ስራዎችን አበርክተዋል። “ጁሊየስ ቄሳር”፣ “ዋናው ተቆጣጣሪ” የተሰኙ ቲያቶችን ተርጉመው ለመድረክ አብቅተዋል። “ከለንደን አዲስ አበባ” የሚል ወጥ ቲያትር ጽፈው ለመድረክ ያበቁት አሰፋ ገብረማርያም በቀድሞ መንግስት “ኢትዮጵያ ቅደሚ” የሚለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር አበርክተዋል። የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርን ዋና ፀሐፊ በመሆን ማገልገላቸውንም የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል ። በስደት ሕይወታቸው በኢትዮጵያ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩም ተመልክቷል። |