ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያን ምርጫ ሂደት በማበረታታት ስህተት መሥራቷን ፍሪደም ሀውስ ገለጸ።

ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

ፍሪደም ሀውስ  ይህን ያለው-በዩናይትድ ስቴትስ  ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ  ወንዲ ሸርማን ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ አስመልክተው ለተናገሩት ንግግር በሰጠው ምላሽ ነው።

ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደኾነች የጠቀሱት ወንዲ ሸርማን  ሀገሪቱ በመጪው ግንቦት  የምታደርገው ምርጫ  ነጻ፣ፍተሀዊና ተዓማኒ እንደሚሆን  በእርግጠኝነት  ተናግረዋል።

“ወንዲ ሸርማን የተናገሩት ነገር መሉ በሙሉ በመረጃ ላይ ያልተመሰረተና  መጥፎ ውጤት የሚያስከትል  ነው”ብለዋል- የፍሪደም ሀውስ ምክትል ፕሬዚዳንት ዳንኤል ካንጌርት።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም፦ “ኢትዮጵያ-በዋነኝነት  ኢ-ዲሞክራሲያዊ ከሆኑት የአፍሪካ  ሀገሮች መካከል አንዷ ሆና ቀርታለች። ሸርማን ምርጫውን ተዓማኒ ብለው በመጥራት  የኢትዮጵያን መንግስት

ማበረታታታቸው፤  ለዜጎቹ ዲሞክራሲያዊ መብት ፈጽሞ ክብር አለመስጠት ነው” ብለዋል።

ይልቁንም መንግስት የታቃውሞ ድምጾችን ሁሉ  ለመጨፍለቅ እየተከተለ ያለውን የአፈና መንገድ  ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው-ብለዋል ሚስተር ዳንኤል።