መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፖሊዩ ቫይረስ በተከሰተበት አካባቢ ሳይታወቅ ጉደት አድርሶዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት በበሺታው መጠቃታቸውን በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡
በሐገራችን ኢትዩጵያ እና አጎራባች አገሮች የተከሰተውን የፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የፖሊዩ ቫይረስ መከላከያ ክትባት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሀገሪቱ ባለፉት አስር አመታት በህጻናት ላይ የሚከሰቱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሽታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ስኬታማ ሁኛለሁ ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ቢናገርም ችግሩ ገና ያልተነካ እንደሆነ በተባባሰ ሁነታ ገንፍለው የሚነሱ ወረርሺኙች አመላካች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ባለፉት አምስት አመታት የፖሊዮ በሽታ በሀገሪቱ ተከስቶ እንደማያውቅ ተጠቅሷል በተቃራኒው የአለም ጤና ድርጅት ግን ከበሺታው ሐገሪቱ አለመጽዳቱዋን ሲያሳውቅ ከርሙዋል።
በሽታው በኢትዩጵያ ፤በሶማሊያ በወረርሺኝ መልክ መከሰቱን የጠቀሱት የሚንስትር መስሪያ ቤቱ ሀላፊዎች ችግሩ እንዳይባባስ ይሄው ተግባር ይከናወናል ብለዋል።
እድሜያቸው ከ15 አመት በታች ለሆኑና ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ህጻናት ክትባት እየተሰጠ ነው።በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊዩ ቫይረስ መከላከያ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ። ክትባቱ ከመስከረም 23 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።ቢልም በኦሮምያ ፤ በደቡብ፤ በአማራ ፤ እና በሌሎች ክልሎች በትራንስፖርት ችግር በጊዜው ለማድረስ አለመቻሉ እና መዳህኒቶች ችግር እበንደገጠማቸው በተደጋጋሚ ሪፖርት እየጠደረገ ነው፡፡
በክትባት ዘመቻው ከ13 ሚሊየን በላይ ህጻናት ይከተባሉ ተብሎ ቢገመትም የታሰበውን ያህል ስኬታማ ለማድረግ የሎጀስቲክ አቅርቦት ፈታ|ኝ ሁኖወዋል፡፡ ሲል ለሚኒሰተር መስሪያ ቤቱ የሚደርሱ የክልል እና የወረዳ ሪፖርቶች አመልክተዋል፡፡
ይህን ተከተሉ የተወሰደ እርምጃ ምንም የለም፡፡