የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ 13 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል አቃቤ ሕግ የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው።
በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች አቶ ሉሉ መሰለን ጨምሮ አቶ ዓለም ክንፈ፣ ወ/ሮ አየለች አበበ ፣ አቶ በጋሻው ዱንጋ፣ አቶ በረከት ተገኔ ፣ አቶ ደረጀ አደመ ፣ አቶ ዘኪዮስ ዘሪሁን አቶ ጌታሁን ቃጻ አቶ ሲሳይ አምባው አቶ መርዶኪዮስ ሽብሩ አቶ መሀመድ ዳና ፣ አቶ አጥናፉ አበራ እና አቶ ያረጋል ሙሉዓለም ናቸው፡፡
በተጨማሪም የጸረ ሽብር አዋጁን አንቀጽ 7 እዝባር 1 ተላልፈዋል በሚል በፌደራል አቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸዋል።
ተከሳሾች ከአርባ ምንጭ ከተማ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርገው ከዛሬ አራት ወራት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ነገረ ኢትዮጵያ አክሎ ዘግቧል።