የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እየተከበረ ነው

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎርጎሪያን ካላንደር የሚቆጥሩ አገሮች አዲስ ዓመታቸውን በልዩ ድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ።

በጎርጎሪያን ቀመር መሰረት ኢየሱስ  በዳዊት ከተማ በኢሩሳሌም በምትገኘው ቤተ-ልሔም ከተወለደ 2014 ዓመት ሆኖታል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አዲስ ዓመትን ከሁሉም ቀደም ብላ የተቀበለችው አገር  ኒውዚላንድ ነች።

ቤጅንግን ጨምሮ የምስራቅ እስያዎቹ  ጃካርታ እና ሲንጋፓር አዲስ ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋል ።