የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ

የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )በሳውላ ዶ/ር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ ህዝቡ ያቀረባቸው የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዲሟሉለት ጠይቋል።
የአስተዳደር ወሰን ፣ የሹመት እንዲሁም መንገድን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ጥያቄያቸውን መንግስት እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ጥያቄ አቀርበዋል።
ህዝቡ ለውጡን ለሚመሩት የኢህአዴግ መሪዎች እና ለተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ያለውን ድጋፍም የተለያዩ ፎቶዎችን በመያዝ ድጋፉን ገልጿል።