የጎንደርን ህዝባዊ እምቢተኝነት በአጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)

በጎንደር ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ  የሚኖሩ ዜጎች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ። ይህ ዜና እየተጠናከረበት ባለበት ሰዓት በጎንደር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት መንገድ መዝጋቱ ታውቋል።

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመከለክተው እስካሁን ድረስ በትንሹ አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል። ሌሎች በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ስለሁኔታው መረጃ የደረሳቸው በጎንደር እና አካባቢው የሚኖሩ የታጠቁ አርሶ አደሮች ወደ ከተማ እየገቡ እንደሆነ የደረሰን መረጃ የመለክታል።

ከአዲስ አበባና ባህር ዳር ከተሞች እንዲሁም ወደጎንደር የሚገቡ ሌሎች መንገዶችም ዝግ መሆናቸውን ለኢሳት ከደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።