(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 29/2010) የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በሃገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ የማሸነፍ እድላቸውን ማረጋገጣቸው ታወቀ።
ጠንካራ የሚባሉት ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን ተከትሎም በተቃዋሚዎች ዘንድ መራጮች ድምጽ እንዳይሰጡ ጥሪ መደረጉን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።
ለ 3 ቀናት በተካሄደው በዚህ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተመዝግበው ድምጽ ያልሰጡ መራጮች ከ 500 – 28 ፖውንድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።
የሀገሪቱ ህግ ለምርጫ የደረሰ ማንኛውንም ሰው ድምጽ እንዲሰጥ ያስገድዳል ያለው ዘገባው ከዚህም በተጨማሪ ድምጽ ሰጪዎች ድምጽ እንዲሰጡ የተላያዩ ማባበያዎች መደረጋቸውም ተመልክቷል።
ከወጣት እስከ አዛውንት ተሳትፈውበታል በተባለው በዚህ ምርጫ በእስካሁኑ ሂደት አል ሲሲ የማሸነፍ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
የምርጫው ውጤት ሰኞ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።