የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል