የጋና ፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው፤ የ 68 ዓመቱ  ፕሬዚዳንት ጆን አታ   ዛሬ ከቀትር በሁዋላ  ሀመም በተሰማቸው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነው  ህይወታቸው ያለፈው።

ይሁንና  ፅህፈት ቤቱ ዝርዝር ሁኔታውን ከመግለጽ ተቆጥቧል።

“የጋና ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትን ድንገተኛና ያልተጠበቀ  ሞት ስንገልጽ በጥልቅ ልባዊ ሀዘን ነው” በማለት ነው ፅህፈት ቤቱ የፕሬዚዳንት ሚልስን  ሞት ይፋ ያደረገው።

የአፍሪካ የዲሞክራሲ ምሳሌ  የሆኑት የፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ሞት  መሰማት፤ በጋና ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ታውቋል።

ምዕራባዊ አፍሪካዊቱን አገር ከ 2009 ጀምሮ ሲመሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት ጆን አታ  የጉሮሮ ካንሰር ህመምተኛ ነበሩ።

ዲሞክራሲያዊ መንግስትን በማቆም የምትወደሰው ጋና፤ ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ማግስት   የጎበኟት ብቸኛ  አፍሪካዊት አገር መሆኗ ይታወቃል።

በቅርቡ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በቡድን 8 አገራት ስብሰባ ላይ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ፣ ጆን አታሚል ከአቶ መለስ ጎን ተቀምጠው በትዝብት ይመለከቱ ነበር።

ሁለቱም የአገር መሪዎች ከቡድን 8 ስብሰባ በሁዋላ መታመማቸው ዜናው የተለየ ትኩረት እንዲያገኝ ያደርገዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide