የጃዊ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በእሳት ተቃጠለ

ኅዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በመገንባት ላይ ያለው እና ከመጠናቀቂያ ጊዜው ለአንድ አመት ያክል የዘገየው የስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነ 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ሙሉ በሙሉ በእሳት ጋይቷል። ድርጊቱን ማን እንደፈጸመው በስም ያልጠቀሱዋቸው አካላት እያጣሩት ነው ሲሉ፣ የጠቀሱት የፋብሪካው ሃላፊ አቶ ባይነሳኝ፣ ጥናቱ ሳያልቅ መንስኤውን ይፋ ማድረግ አይቻልም ይላሉ።

ሌሎች ወገኖች ደግሞ ድርጊቱ ተቃውሞን ለመግለጽ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላሉ። ነዋሪዎችን በማፈናቀል የተጀመረውን ፕሮጀክት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲቃወሙት ቆይተዋል። ጥናቱ ሳይጠናቀቅ የደረሰውን ጉዳት በገንዘብ ለመተመን እንደማይቻል አቶ ባይነሳኝ ገልጸዋል። የፋብሪካው ስራ በመጓተቱ የተነሳ ከሁለት አመት በፊት ድርጅቱ ሸንኮራ አገዳ ለማቃጠል ተገዶ ነበር።