የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፍርድ የማሰማት ሂደት ለሰኞ ተራዘመ

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የኮሚቴው አባላት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በችሎቱ ቢታደምም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የማሰማቱን ሂደት በድጋሜ ወደ ሰኞ አራዝሟል።
ችሎቱ የአቃቢ ህግ መስክሮችን ቃል አንብቦ ከጨረሰ በሁዋላ ተከሳሾች ለፖሊስ ሰጡት ያለውን ቃል በንባብ አሰምቷል። የፊታችን ሰኞ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በዛሬውም ችሎት ከትናንት ባልተናነሰ ሁኔታ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ነበር።