የደቡብ ክልል ወጣቶች “የደህዴን ኢህአዴግ አገዛዝ በቃን” ሲሉ ተናገሩ

የካቲት ፳፫ ( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህዴን የወጣቶች ሊግ ከመላው የደቡብ ክልል ወጣቶችን አበል ከፍሎ በወልቂጤ ከተማ በማሰባሰብ፣ የክልሉን ሰላምና እና እድገት ለመስበክ ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል። “የመንግስቱ ሚዲያዎች ሁሉ ሀሰተኛ ናቸው፣ መንግስትንም ለማጥፋት የኛ እጅ በቻ በቂ ነው” በማለት አንዳንድ ወጣቶች ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ “ደህዴን ምንም አልሰራም፣ ክልሉን ወደ ኃላ ያስቀረ እና በድህነት እየመራ ያለ ነው በመሆኑ ሊበቃው ይገባል” በማለት በድፍረት ተናግረዋል።