የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በናጀሪያዊው ስደተኛ ላይ ያደረሱት ጥቃት ቁጣን ቀሰቀሰ

ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬፕታውን የሚገኙ ፖሊሶች በአንድ ናይጀሪያዊ ስደተኛ ላይ ያደረሱት ጥቃት በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ከተለቀቀ በሁዋላ የአለም ህዝብ ቁጣውን እየገለጸ ነው።

የደቡብ አፍሪካዊ ፖሊስ ድረጊቱን የፈጸሙ ሁለት ፖሊሶች መታሰራቸውን ቢገልጽም የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ግን የደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች በተለይም በስደተኞች ላይ የሚያደርሱት እንግልት ለከት እያጣ መጥቷል ይላሉ።

የደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች ከውጭ አገር ስደተኖች ገንዘብ እንደሚቀበሉ፣ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደና ያልሆኑትም እስከ ማሰር እንደሚደርሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።