የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር መምህራኑን ለማስፈራራት እየሞከረ ነው

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወረዳው መምህራን እንደሚሉት ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ ያለፈቃዳቸው 30 በመቶ ተቆርጦ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሊሰጥባቸው መሆኑን በመቃወም ፊርማቸውን አሰባስበው ካስገቡ በሁዋላ ፣ ሚስጢራችንን “ለጸረ ሰላም ሃይሎች አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል” በሚል ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው። መምህራኑ ማስፈራሪያውን ወደ ጎን በማለት አሁንም በአቋማቸው በመጽናት ጥያቄያችን ይመለስልን በማለት እየተጠየቁ ነው።
በመጋቢት ወር መምህራኑ ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ወረዳው ደሞዝ መቁረጡን አቁሞ ነበር። ይሁን እንጅ የትምህርት መዝጊያ ሰአቱን ምክንያት በማድረግ እና መምህራን ይበታተናሉ በሚል ስጋት የሰኔ ወር ደሞዛቸውን ለመቁረጥ ያደረገው ሙከራ መምህራኑን አበሳጭቷል።