ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት ድርጅቱ ራሱን እንደ ሁለተኛ መንግስት በመቁጥር የጦር መሳሪያዎችንና አማጽያንን አስጠልሏል በማለት ነው።
ፕ/ር ሳልቫኪር የተመድ ዋና ጸሀፊ አገሪቱን ማስተዳደር የሚፈልጉ ከሆነ በግልጽ ይንገሩን ያሉ ሲሆን፣ ተመድ ወደ አገራቸው ሲገባ ተጓዳኝ መንግስት ሆኖ መግባቱን አላውቅም ነበር ብለዋል።
ተመድ በበኩለ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የቀረበውን ወቀሳ አልተቀባለውም። ድርጅቱ ትጥቃቸውን ይዘው የሚመጡ ወታደሮችን ትጥቅ እያስፈታ መጠለያ እየሰጠ መሆኑን ና መሳሪያዎችንም ለማስረከብ ከመንግስት ጋር ድርድር ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
በዩጋንዳ ጦር እየታገዙ ድል የቀናቸው ኪር፣ ከአማጽያን የሚቀርብላቸውን ቅድመ ሁኔታ አልተቀበሉም። የዩጋንዳ ጦር እንዲወታ እንዲሁም ያሰሩዋቸውን 11 ሰዎች እንደማይፈቱ ግልጽ ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ፣ ለምክትላቸው ምህረት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውንም አልሸሸጉም። በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሰላም ድርድር ብዙም ውጤት ሊያመጣ አለመቻሉን የመገናኛ ብዙሀን ይገልጻሉ።