የደህንነት ሰራተኛው ለኢሳት ሚስጢራዊ መረጃ ሰጥተሃል በሚል ታስሮ እየተሰቃየ ነው

ሚያዝያ ፲ (አሥር) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ኢጄንሲ (ኢንሳ) ውስጥ የደህንነት ሰራተኛ የሆነው ጸጋየ ተክሉ የተባለ ግለሰብ ለኢሳት መረጃ ታቀብላለህ በሚል በቂሊንጦ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል። ጸጋዬ በ2003 ዓም በመረጃ መረብ ውስጥ በሚሰራበት ወቅት ከኢሳት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የድርጅቱን ሚስጢር ለኢሳት ሰጥቷል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፣ በማስረጃነትም ኢሳት ከሌላ ግለሰብ ጋር ያደረገውና የራሱ ያልሆነ የድምጽ ማስረጃ ቀርቦበታል። ክሱ ከሌሎች እስረኞች እንዲነጠል ተደርጎ በዝግ ችሎት እየታየ መሆኑም ታውቋል። አቶ ጸጋየ አቃቢ ህግ በማስረጃነት የቀረበው ድምጽ የእርሱ አለመሆኑን ቢናገርም የሚሰማው አካል አላገኘም።
በቃሊቲና በቂልንጦ ለኢሳት መረጃ ሰጥታችሁዋል በሚል ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች ታስረው ይገኛሉ።