የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት ከአገር እንዳይወጣ ታገደ

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም ዓለማቀፍ የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የነጻነት ሽልማት በሲቲዝን ጆርናሊዝም ጋዜጠኝነት ምድብ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ የሆኑትን ዞን 9 በመወከል ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሽልማታቸውን ለመውሰድ ወደ ፈረንሳይ ሊያደርገው የነበረው ጉዞ በኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች ፓስፖርቱን በመነጠቁ መታገዱ እንዳሳሰበው ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ገልጿል። ”የጉዞ እገዳው በዘላለም ክብረት ላይ መጣሉ በጣም አሳስቦናል አስገርሞናልም” በማለት የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ክሌያ ኻህን ሰርበር ተናግረዋል።
ዘላለም ክብረት ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ቤት ካሳለፈ በሁዋላ ሃምሌ ወር ላይ ነጻ ተብሎ ተለቋል።