የዝምባብዌ ፍርድ ቤት ኢመርሰን ምናንጋዋን የምርጫ ውጤት አጸደቀ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ፍርድ ቤቱ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ኤም ዲ ሲ ፓርቲ ያቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ያደረገው ሲሆን፣ ዳኛ ሉኬ ማሌባ በተቃዋሚዎች የቀረበው ክስ በተጨባጭ መረጃ የተደገፈ አይደለም ብለዋል።
የምርጫውን ውጤት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ 6 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል። ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን ከተወገዱ በሁዋላ የተደረገው የመጀመሪያው ምርጫ አንዳንድ ችግሮች የነበሩበት ቢሆንም፣ ከሞላ ጎደል ነጻ ነበር ተብሎአል።
ኤም ዲ ሲ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ይቀበል አይቀበል እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።