የወጣቶችን ፈንድ በአስቸኳይ ለማከፋፈል እንቅስቃሴ ተጀመረ

የወጣቶችን ፈንድ በአስቸኳይ ለማከፋፈል እንቅስቃሴ ተጀመረ
(ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)በአገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ተቃውሞውን ሊቀንስ ይችላል በሚል የተመደበው የወጣቶች የስራ ማስያዣ በጀት በአፋጣኝ ጥቅም ላይ እንዲውል ትዕዛዝ በመተላለፉ ሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ወከባ ውስጥ መውደቃቸው ታውቋል።
ገንዘቡ ከተመደ በሁዋላ የባለስልጣናት ቤተሰቦችን ኪስ ከማደለብ ውጭ የፈየደው ነገር እንዳልነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች የሚገኘው ቀሪ ገንዘብ ከነውስብስ ችግሩም ቢሆን ይሰራበት የሚል ትዕዛዝ ከወረደ በሁዋላ የፈንዱ አስተባባሪ ተቋማት ትንፋሽ አጥተው ገንዘቡ ስራ ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ እየተሯሯጡ ነው።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ለወጣቶች በቂ ገንዘብ እንደተመደበ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ተቃውሞውን ለማብረድ መታሰቡን ምንጮቻችን ገልጸዋል።