ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከ60 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ የዘመቱ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከኮሪያ መንግሰት ጡረታ ሊቆረጥላቸው እንደሆነ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ጊዮን ኪም እንዳሉት ፥ የጡረታውን አበል የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለመቁረጥ የፈለገው ለሀገሪቱ ነጻነት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ያደረጉትን ትልቅ ተጋድሎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
በዚሀም መሰረት አርበኞቹ በየወሩ ሰባት መቶ ብር እንደሚከፈላቸው አምባሳደሩ ጠቁመዋል።
ከጡረታው አበል በተጨማሪ የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለ300 የዘማች ቤተሰቦች በቀጣዩ ሶስት ዓመት ውስት የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥም አምባሳደሩ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ፦”የኮሪያን መንግስት ውሳኔ፤ለአርበኞቹ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳየ ነው” በማለት አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።
_____________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide