የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የወንጀል ምርመራ ልዩ ክፍል ሃላፊ ኖሃህ ካቱሞ 100 ኢትዮጵያውያን ኬንያን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አማርኛ የሚያስተረጉም በመጥፋቱ በማግስቱ መቀጠራቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል።
አምና በተመሳሳይ መንገድ 95 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
አገራቸውን እየለቀቁ ወደ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ አለመሄዱን መረጃዎች ያመለክታሉ።