መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ተከትሎ የደኅንነት ስጋት እየጨመረ ስለመጣ ኩዌታዊያን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ሲሉ በኢትዮጵያ የኩዌት አንባሳደር ራሽድ አልሃጅሪ አስጠነቀቁ። ኩዌታዊያን በኢትዮጵያ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጉዞዎች እንዲሰርዙና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትም ዜጎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች በአፋጣኝ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲሉ አንባሳደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በመላው ኢትዮጵያ እሁድ እለት ለስድስት ወራቶች የሚቆይ አስቸኳይ የሰዓት እላፊ አዋጅ መታወጁንና አያሌ ዜጎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የኩዌት የዜና አውታር ዘግቧል።