ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጡት፣ ግንባሩ እስካሁን ድረስ ከመንግስት ጋር ድርድር ያላደረገ ቢሆንም፣ በኬንያ መንግስት በኩል የንግግር ጥያቄ እንደቀረበለት ተናግረዋል።
የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ድርድሩ በገለልተኛ አገር መካሄድ እንዳለበት፣ አለማቀፍ ኮሚኒቲው ድርድሩን እንዲመራ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን አቶ ሀሰን ገልጠዋል::
ከብዙ ጊዜ ውይይት በሁዋላ ከመንግስት የቀረበውን የድርድር ጥያቄ መቀበላቸውን የገለጡት አቶ ሀሰን፣ ሁኔታዎች ተመቻችተው እንዳለቁ ድርድሩ ሊጀመር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
አቶ ሀሰን መንግስት የድርድር ጥያቄ ቢያቀርብላቸውም አሁን በኦጋዴን እና በመላው አገሪቱ ህዝብ ላይ የሚፈጽመው ግፍ እንዲህ በቀላሉ ድርድሩን ውጤታማ ያደርገዋል ብለው እንደማያስቡ ገልጠዋል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide