ኅዳር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻአውጪ ግንባር የሃለጋ ክንፍ ታጣቂዎች በዱሁሁን አውራጃ ውስጥ በገጠር መንደሮች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ነበሩ ባላቸው የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።በዱሁሁን በሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አስገድዶ መድፈር፣ ድብደባ እና የጅምላ እስራት ሲፈጽሙ ከነበሩት ውስጥ በደፈጣ ውጊያ 5ቱ መገደላቸውንና 7 ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን የግንባሩ ወታደርዊ ክንፉ ገልጿል።
አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በሰላማዊው የኦጋዴን ሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን ሰቆቃዎች ከቀድሞው በከፋ ሁኔታ አጠናክረው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በፊቅ እና ጋርቦ አውራጃዎች ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣቶችን በግፍ ገለው ሌሎች ሁለት ደግሞ አቁስለዋል። በተጨማሪም ወጣቶች በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች የሚካሄዱትን ሕዝባዊ አመጾች እንዳይቀላቀሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች በፊቅ እና ጋርቦ አውራጃዎች ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣቶችን በግፍ ገለው ሌሎች ሁለት ደግሞ አቁስለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታ ሃይሎች በተለይ በቃሩድ፣በሸበሌ፣ ሽኒሌ፣ ዳናን፣ ቢርቆት እና ጉዲስ የጅምላ እስራቱን አጠናክረው ቀጥለዋል።የአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች ግን በሁኔታዎቹ ሳይደናገጡ በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ንቅናቄ አብዮት እንደሚደግፉ እና ለብሄራዊ ለውጡ አጋዥ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በቀጠናው ከ2007 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እየፈጸመ መሆኑን ግንባሩ ገልጾ በወታደራዊ ክንፉ እርምጃ የተወሰደባቸውን፣ የቆሰሉትን እንዲሁም የታሰሩትን ዘርዝሮ አቅርቧል።