የኦሮሞ አባገዳዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 17/2011) የጋሞ የሃገር ሽማግሌዎች አርባምንጭ ለመጡት የኦሮሞ አባገዳዎች ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው።

በቅርቡ በቡራዩ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ወደ አርባምንጭ የተጓዙት የኦሮሞ አባገዳ አባቶች ለጋሞ የሃገር ሽማግሌዎች ምስጋና ማቅረባቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የቡራዩን ጥቃት ተከትሎ በአርባምንጭ በተነሳ ተቃውሞ የጋሞ አባቶች ብሄር ላይ ያተኮረ የንብረትና የሰው ህይወት ጥቃት እንዳይፈጸም ያደረጉት ተግባር በአባገዳዎች ዘንድ በአድናቆት ተነስቷል።

የኦሮሚያ ክልላዊ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳም ለጋሞ አባቶች ምስጋና ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።