የኦሮሞ ተዋጊዎችን በማሳደድ ቄዳር እና ማራ-ዲሌ ወደ ተባሉ የሶማሊያ አካባቢዎች ድንበር አቋርጦ የገባዉ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን፤ ኦል አፍሪካን የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ሰራዊቱ በአካባቢዉ የሚያደርገዉን አሰሳ አጠናቆ ከአንድ ቀን በሁዋላ ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን የገለፁት፤ የአካባቢዉ የአይን ምስክሮች እንደሆኑ የዜና አግልግሎቱ ገልጿል።
የማእከላዊ ሶማሊያ ከተሞችን ይዞ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ድንበር አቋርጦ የገባዉ፤ ለዘብተኛ የሆነዉ የአህሉ ሱና ወል-ጀማ ቡድን መሪዎች ፤በአዲስ አበባ ተገኝተዉ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች ጋር የአካባቢዉን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከተነጋገሩ በሁዋላ እንደሆነ ታዉቋል።
የኢትዮጵያ መንግሰት ወታደሮች፤ የሶማሊያ ታጣቂዎችን ለመምታት በተደጋጋሚ የሶማሊያን ድንበር እንደሚጥሱ ይታወቃል።