ግንቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሆኖም ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጬውን ሰነድ እንደማያውቀው አንድ የክልሉ ባለሥልጣን ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሰንደቅ እንደገለጹት ፣ ኦህዴድና የክልሉ መንግስት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 49 ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት የልዩ ጥቅምን አተገባበርን በተመለከተ መካተት አሉባቸው ያሏቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መብቶችን በዝርዝር ለሚመለከተው አካል አስተላልፈዋል።
“ክልሉ ከአዲስ አበባ ማግኘት ይገባዋል የተባለን ጥቅም የሚዘረዝርና ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ሢሰራጭ የከረመውን ረቂቅ ሰነድ ያዘጋጀው ክልሉ ነውን?ካልሆነስ ስለሰነዱ ምን ይላሉ?” ተብለው የተጠየቁት አቶ አዲሱ፦ “ወደ ኋላ ሄጄ የተዘጋጀው ሰነድ ነው፤ ረቂቅ ነው የሚባለውን አላውቅም።ረቂቅ ሰነድ እንዴት በዚህ በኩል ወደ አደባባይ እንደሚወጣ የምናውቀው የለም።እንዲሁም ኦህዴድ ነው ያዘጋጀው ስለሚባለው ነገር ረቂር የማዘጋጀት ሥራ የኛ ተግባር ባለመሆኑ አስተያዬት ለመስጠት እንቸገራለን”ብለዋል።
አቶ አዲሱ በመጨረሻም ህግ የማውጣት ሥልጣኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመሆኑ በዚህ ጉዳይ የምንሰጠው አስተያዬት የለም ብለዋል።