የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ም/ል ሊቀመንበሩ አቶ ዓለማየሁ መኮንን በትናንትናው ዕለት ‹‹የፍትህ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው›› በማለት ስለዞኑ ፍትህ መናገራቸውን ተከትሎ ታስረው ነበር፡፡ ‹‹ፍትህ በሌለበት፣ነጻነት አይኖርም ፣ነጻነት በሌለበትም ፍትህ አይኖርም ›› ብለው ተናግረዋል በሚል በዳኛ ዳዊት አድማሱ ጥሩነህ በቀረበባቸው አቤቱታ መታሰራቸው በፖሊስ የእለት መዝገብ ላይ ሰፍሮ ቢገኝም፣ ማንም ቀርቦ ስለሁኔታው ሊያስረዳ ባለመቻሉ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሸጎሌ ሾዴ ከታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመምጣት እንዳስፈቷቸው ለማረጋጋጥ መቻሉን ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ ገልጿል።
አቶ ዓለማዬሁ በአካባቢያቸው የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በድፍረት በማጋለጥ ይታወቃሉ።