የእንግሊዝ ፖሊስ በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ ክስ መሰረተ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ታደሰ ክስ የተሰመረተባቸው በጥር ወር ኤርትራ ቆይተው ወደ እንግሊዝ ሲገቡ፣ አየር ማረፊያ ላይ በተደረገው ፍተሻ አንዳንድ ጽሁፎችን ከዌብ ሳይት ላይ ወስደው ኮምፒተሮቻቸው ላይ አውርደውና ቦርሳቸው ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው ነው። ጽሁፎቹ በእንግሊዝ ፖሊሶች በጥርጣሬ መታየታቸውን ተከትሎ፣ ክስ እንደተመሰረተባቸው ታውቋል። ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲሞክራሲና የፍትህ ትግል ውስጥ በአርበኞች ግንቦት 7 ውስጥ በአመራርነት በማገልግል ላይ ናቸው።
የእንግሊዝ ፖሊሶች ውሳኔ ከአርበኞች ግንቦት7 የትግል አላማና ስትራቴጂ ጋር የተያያዘ ነገር እንደሌለው የድርጅቱ አመራሮች ገልጸዋል።
ገዢው ፓርቲ የእንግሊዝ መንግስት አርበኞች ግንቦት7ትን በሽብርተኝነት እንዲፈርጀው ያቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሜሪካ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም መውሰዱ ይታወቃል።