ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የደህንነት ዋስትናቸውን በተመለከተ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ምንም እንኳ ከ10 ቀናት በሁዋላ ተቋርጦ የነበረው የኢንትርኔት አገልግሎት መልሶ ቢመጣም፣ አገልግሎቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ እንደሚችል በማስጠንቀቅ፣ ዜጎቹ ሌሎች የስልክ የመገናኛ አማራጮችን እንዲጠቀሙ አስጠንቅቋል። የእንግሊዝ ኢምባሲ በኢንተርኔት መቆራረጥ የተነሳ በቂ አገልግሎት መስጠት አለመቻሉንም ገልጿል። ኢትዮጵያ በምታዋስናቸው ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ድንበሮች መጓዝ አደገኛ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም እንዲሁ ተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።