የእስቴ መምህራን ተቃውሞ አሰሙ

ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ  መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ታጅቦ መበተኑንና የመምህራኑ  ያለተጠበቀ እርምጃ የአካባቢውን ባለስልጣናት ማስደንገጡን መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል።