የኤርትራው ፕሬዝዳንት በጎንደር ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 30/2011) የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

በተመሳሳይ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት አብዱላሂም በተመሳሳይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ሶስቱ መሪዎች ጎንደር የተለያዩ ስፍራዎችን ጎብኝተው ከሰዓት በኋላ ባህርዳር ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ፣የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች በአስመራ የጀመሩትን የሶስትዮሽ ውይይት በበህርዳር ከተማ ለመቀጠል መግባታቸው ተመልክቷዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂን ጎንደር ላይ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ጋር በመሆን የተቀበሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ባህርዳር ከተማ ላይ  ሁለቱን መሪዎቹን ራሳቸው በሚያሽከረክሩት መኪና ይዘው ወደ ስብሰባ ቦታቸው ማምራታቸው ተመልከቱዋል።

ሶስቱ መሪዎች በመስከረም ወር መጨረሻ አስመራ ላይ የጀመሩትን የሶስትዮሽ ውይይት ለመቀጠል መገናኘታቸውም ታውቋል።