የኢጋድ የፖለቲካ አማካሪ ኮለኔል ገብረእግዚአብሔር አለምሰገድ ከሃላፊነት ተነሱ

(ኢሳት ደሴ–ሰኔ 18/2010) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የፖለቲካ አማካሪውን ማባረሩን አስታወቀ።

የህወሀት ኮለኔል የሆኑት ገብረእግዚያብሄር አለምሰገድ ከዛሬ ጀምሮ ከኢጋድ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪነት መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

በኢጋድ ሴክቴሪያት አምባሳደር ማህቡብ ማሊም የተጻፈው ደብዳቤ ኮለኔል ገብረእግዚያብሄር አለምሰገድ ከዛሬ ሰኔ 18 ጀምሮ በእጃቸው የሚገኙ ንብረቶችን አስረክበው እንዲሰናበቱ የሚጠይቅ ነው።

ኢጋድ ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔርን በምን ምክንያት እንዳባረረ ግን አልገለጸም።