የኢድ አል ፈጥር በአል በመላው አለም እየተከበረ ነው

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አለም የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች 1 ሺህ 437ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እያከበሩ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም በአሉን በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች አደባባዮች በመሰባሰብ በጋራ ያከበሩ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ እና በአርሲ ሙስሊሜ ከበአሉ በሁዋላ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ አሰምቷል።

ሰሞኑን በኢራቅ፣ ሳውድ አረቢያና ባንግላዲሽ የደረሱት  ፍንዳታዎች በኢድ አል ፈጥር በአል ድምቀት ላይ ተጽእኖ ቢፈጥሩም፣ በሶሪያ 72 ሰአታት የተኩስ አቁም በመደረጉ የአገሪቱ ሙስሊሞች በአሉን በሰላም እንዲያከብሩ ረድቷቸዋል።