የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችን የኢሜል መልእከቶች እና ሌሎችንም የመገናኛ ዘዴዎች በመሰለል ክስ እየቀረበበት የሚገኘው የኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን ጋር ውል በመዋዋል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እያካሄ ነው።
ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር የ70 ሚሊዮን ብር የኢንፎርሜሽን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ውል ተዋውሎ ስራ በመስራት ላይ ሲሆን፣ በአዋሳና ሌሎችም ዩኒቨርሰቲዎች ተመሳሳይ ስራዎችን እየሰራ ነው።
ድርጅቱ የመንግስት የመረጃ መሰብሰቢያ ተቋም ሆኖ እንዲህ አይነቱን ስራ መስራቱ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚካሄዱ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ተብሎ የሚሰራ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ኮምፒዩተሩ መሰለሉን ተከትሎ በኢንሳ ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።