ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን በኩል አቋርጠው የሚገቡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስጋት ፈጥረውብኛል በሚል የሱዳን መከላከያ
ሰራዊት አስፈላጊውን የድንበር ጥበቃ እንዲያድርግ ሲወተውት የቆየው የኢህአዴግ መንግስት፣ በቅርቡ በሁለቱ ድንበሮች አካባቢ የጋራ ጦር ለማሰማራት
የደሰበትን ስምምነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማድርግ ሰሞኑን አዲስ የጸጥታ ስምምነት ተፈራርሟል። በዚሁ የጸጥታ ስምምነት መሰረት ሁለቱን ድንበሮች
የሚጠብቅ ጥምር ጦር በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ይሆናል። ወታደራዊው እዙን በዙር የመምራት እቅድ እንደሚኖር ቢጠበቅም፣ የመጀመሪያውን ዙር
የትኛው አገር እንደሚመራው የታወቀ ነገር የለም። ሱዳን የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ወደ ድንበሯ እየገቡ የሚፈጽሙትን ጥቃት የኢትዮጵያ መካለከያ
ሰራዊት እንዲከላከልላት ትፈልጋለች። በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት መሬታችንን ለሱዳን ሰጥቶብናል በማለት
የሚከራከሩ ሲሆን፣ አልፎ አልፎ ወደ ውስጥ እየገቡ የተለያዩ ጥቃቶችን ይፈጽማሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ተቃዋሚዎች ሱዳንን እንደመሸጋገሪያ
በመጠቀም በመንግስት ላይ ጥቃት ለመፈጸም እየተደራጁ ነው ብሎ ይከሳል።