የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆሉ ተዘገበ

ነኅሴ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ3.25 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን የንግድ ሚኒስቴርን በመጥቀስ ኒው ፎልቶን ዘግቧል።
አሁንም አገሪቷ ወደ ውጭ አገራት ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ ቡና ቀዳሚነቱን እንደያዘ ሲሆን፣ ከቡና ሽያጭ ገቢ 780 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 8.5 % ጭማሪ አሳይቷል።
የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል ዋናው ምክንያቶች የምርት ግብዐት እጥረትና የዓለም ገበያ ዋጋ አለመረጋጋት ቀዳሚ ምክንያቶች መሆናቸውን የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን ሪፖርት ጠቅሶ ኒው ፎልቶን ዘግቧል።
ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማስገባት ታቅዶ ከዕቅድ በታች ገቢ መገኘቱ በአገሪቱ የምርት ግብዐት እጥረት መከሰት ዋናው ምንጭ ከዐቅም በላይ ማቀድና የተሳሳተ ምጣኔሃ ብታዊ ፖሊሲ ውጤት መሆኑን የሙያው ጠበብቶች ይጠቁማሉ።